ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ማህበረሰብ
ከ5 እስከ 11 አመት ለሆኑ ህጻናት Pfizer's የኮቪድ-19 ክትባት በሚቀጥሉት ቀናት ለአስቸኳይ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውል ይፈቀዳል ተብሎ ይጠበቃል። ክትባቱ ከተገኘ በኋላ MCPS ከካውንቲው የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት እና ከቀይ መስቀል ሆስፒታል ጋር በመሆን በርካታ ነፃ የክትባት ክሊኒኮችን በት/ቤቶች እና በካውንቲው የተለያዩ ቦታዎች ለማቅረብ በትብብር ይሠራል።
የክሊኒክ ቀናት፣ ሰአቶች እና ቦታዎች በቅርቡ ይገለጻሉ። የኮቪድ-19 ክትባት ያላገኙ እና ክትባት ወይም booster ለመውሰድ የሚፈልጉ ወላጆች/አሳዳጊዎች በእነዚህ ክሊኒኮች ሊወስዱ ይችላሉ።
ክትባቶች ከብዙ ሥፍራዎች ማለትም፦ የማህበረሰብ እና የት/ቤት ክሊኒኮችን ጨምሮ፣ የሕፃናት ሐኪሞች፣ ፋርማሲዎች፣በመሣሰሉት ቦታዎች ለማግኘት እንደሚቻል ይጠበቃል። ወላጆች የቀጠሮ መርሐግብርን በተመለከተየሕፃናት ሃኪሞቻቸውን እንዲጠይቁ በጥብቅ እናበረታታለን።
የኮቪድ-19 ክትባቶች የህጻናትን ደህንነት ለመጠበቅ እና በትምህርት ቤት ለማቆየት ይረዳሉ። ወላጆች ለአጠቃላይ የክትባት መረጃ እና ምን እንደሚጠበቅ ለማወቅ የኮቪድ-19 ክትባቶች ለልጆች እና ለወጣቶች መጎብኘት ይችላሉ ልጆቻችሁን ከክትባታቸው በፊት፣ በሚከተቡበት ጊዜ እና በኋላ ልጆቻቸውን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ልዩ ፍንጭ።
ከ DHHS እና ከቀይ መስቀል ሆስፒታል ጋር ለምናደርገው ትብብር እያመሰገንን ይህንን እድል ለትንንሽ ተማሪዎቻችን እና ለቤተሰቦቻቸው ልናቀርብ ጓጉተናል።
እባክዎን ይህን ቅጽ በማጠናቀቅ ልጅዎ እንዲከተብ/እንድትከተብ ያለዎትን ፍላጎት ያረጋግጡልን።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org